Muslim Flow በሙከራ ላይ ሲሆን በቅርቡ በ Google Play ላይ ይመጣል። አውርድ

ከመብላት በፊት እና በኋላ እና ጾም ሲፈታ የሚባሉ ዱዓዎች

6 አዝካር

ሂደት

ከመብላት በፊት የሚደረጉ ልመናዎች

1 አንድ ጊዜ አንብብ

((إِذَا أَكَلَ أَحَدُكُمْ طَعَاماً فَلْيَقُلْ بِسْمِ اللَّهِ، فَإِنْ نَسِيَ فِي أَوَّلِهِ فَلْيَقُلْ بسمِ اللَّهِ فِي أَوَّلِهِ وَآخِرِهِ)).

(ለመመገብ ስትነሱ እንዲህ በሉ፦(Bismil-lah።) መጀመሪያ ላይ መናገር ከረሳችሁ ደግሞ ባስታወሳችሁ ጊዜ በሉ፦ በመጀመሪያውም በመጨረሻውም በአላህ ስም።)

2 አንድ ጊዜ አንብብ

((مَنْ أَطْعَمَهُ اللَّهُ الطَّعَامَ فَلْيَقُلْ: اللَّهُمَّ بَارِكْ لَنَا فِيهِ وَأَطْعِمْنَا خَيْراً مِنْهُ، وَمَنْ سَقَاهُ اللَّهُ لَبَناً فَلْيَقُلْ اللَّهُمَّ بَارِكْ لَنَا فِيهِ وَزِدْنَا مِنْهُ)).

(አላህ የመገበው ሰው እንዲህ ይበል፦(አላህ ሆይ! በዚህ ባርክልን፤ ከዚህም የተሻለ አብላን።) አላህ ወተት ያጠጣውም እንዲህ ይበል፦(አላህ ሆይ! በዚህ ባርክልን፤ ከዚህም ጨምርልን።))

ከመብላት በኋላ የሚደረጉ ልመናዎች

1 አንድ ጊዜ አንብብ

((الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي أَطْعَمَنِي هَذَا، وَرَزَقَنِيهِ، مِنْ غَيْرِ حَوْلٍ مِنِّي وَلاَ قُوَّةٍ)).

(ይህን ያበላኝና ከእኔ ምንም ኃይልና ብርታት ሳይኖር ያቀረበልኝ አላህ ምስጋና ይገባው።)

2 አንድ ጊዜ አንብብ

((الْحَمْدُ لِلَّهِ حَمْداً كَثِيراً طَيِّباً مُبَارَكاً فِيهِ، غَيْرَ [مَكْفِيٍّ وَلاَ ] مُوَدَّعٍ، وَلاَ مُسْتَغْنَىً عَنْهُ رَبَّنَا)).

(ብዙ፣ መልካም፣ የተባረከ ምስጋና፣ የማያልቅ፣ የማንሰናበተውና የማንተወው የማይቀር ምስጋና ለአላህ ይሁን፤ እርሱ ጌታችን ነው።)(የዚህን ዱዓ ትርጉም በተመለከተ ሌሎች አስተያየቶችም አሉ፤ ከእነርሱ፦ ብዙ፣ መልካም፣ የተባረከ ምስጋና ለአላህ ይሁን። እርሱ የሚበቃ፣ የሚመግብ እንጂ የማይመገብ ነው፤ ከእርሱ ዘንድ ባለው ጭምር የሚናፈቅና የሚፈለግ እርሱ ጌታችን ነው።)

ጾም ሲፈታ የሚደረጉ ልመናዎች

1 አንድ ጊዜ አንብብ

((ذَهَبَ الظَّمَأُ وَابْتَلَّتِ العُرُوقُ، وَثَبَتَ الْأَجْرُ إِنْ شَاءَ اللَّهُ)).

(ጥሙ ሄደ፤ ጅማቶችም ረጠቡ፤ አላህ ቢፈቅድ ምንዳውም ተረጋገጠ።)

2 አንድ ጊዜ አንብብ

((اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ بِرَحْمَتِكَ الَّتِي وَسِعَتْ كُلَّ شَيْءٍ أَنْ تَغْفِرَ لِي)).

(አላህ ሆይ! ነገርን ሁሉ በከበበችው ርኅራኄህ እንድትምረኝ እጠይቅሃለሁ።)

እያንዳንዱን ምግብ በአላህ ስም እና ምስጋና ይጀምሩ እና ይጨርሱ፤ ጾምዎን ሲፈቱም ዱዓውን ይበሉ።

ምንጭ፡ ሒስን አል-ሙስሊም (የሙስሊም ምሽግ)። የአረብኛ ጽሑፍ ከትርጉም ጋር።

ጥያቄዎች

የ«ከመብላት በፊት እና በኋላ እና ጾም ሲፈታ የሚባሉ ዱዓዎች» አዝካር ከየት የመጡ ናቸው?

ከቁርኣን እና ከትክክለኛው ሱንና የተወሰዱ አዝካሮች እና ዱዓዎች ስብስብ ከሆነው ከሒስን አል-ሙስሊም የተወሰዱ ናቸው።

እያንዳንዱ ዚክር ስንት ጊዜ መደገም አለበት?

ቁጥሩ ከእያንዳንዱ ዚክር በላይ ይታያል። ቁጥር በማይታይበት ቦታ አንድ ጊዜ ይባላል።

WhatsApp