ሶላትን ከጨረሱ በኋላ የሚባለው
((أَسْتَغْفِرُ اللَّهَ (ثَلاَثَاً) اللَّهُمَّ أَنْتَ السَّلاَمُ، وَمِنْكَ السَّلاَمُ، تَبَارَكْتَ يَا ذَا الْجَلاَلِ وَالْإِكْرَامِ)).
(አላህን ምሕረት እጠይቃለሁ።(ሦስት ጊዜ) (አላህ ሆይ! አንተ አስ-ሰላም ነህ፤ ሰላምም ከአንተ ነው፤ የልዕልናና የክብር ባለቤት ሆይ፣ ብሩክ ነህ።) (አስ-ሰላም፦ ከጉድለትና ከነውር ሁሉ የጸዳ።))
((لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَحْدَهُ لاَ شَرِيكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ [ثلاثاً]، اللَّهُمَّ لاَ مَانِعَ لِمَا أَعْطَيْتَ، وَلاَ مُعْطِيَ لِمَا مَنَعْتَ، وَلاَ يَنْفَعُ ذَا الْجَدِّ مِنْكَ الجَدُّ)).
(ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፤ እርሱ ብቻውን ነው፣ አጋር የለውም፤ ንግሥናና ምስጋና የእርሱ ነው፤ እርሱም በነገር ሁሉ ላይ ቻይ ነው። አላህ ሆይ! አንተ የሰጠኸውን የሚከለክል፣ አንተ የከለከልከውንም የሚሰጥ የለም፤ ሀብትም ሆነ ሞገስ ለማንም አይጠቅምም፤ ሀብትና ሞገስ ሁሉ ከአንተ ነውና።)
((لَا إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَحْدَهُ لاَ شَرِيكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ، وَلَهُ الْحَمدُ، وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ. لاَ حَوْلَ وَلاَ قُوَّةَ إِلاَّ بِاللَّهِ، لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ، وَلاَ نَعْبُدُ إِلاَّ إِيَّاهُ, لَهُ النِّعْمَةُ وَلَهُ الْفَضْلُ وَلَهُ الثَّنَاءُ الْحَسَنُ، لَا إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ وَلَوْ كَرِهَ الكَافِرُونَ)).
(ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፤ እርሱ ብቻውን ነው፣ አጋር የለውም፤ ንግሥናና ምስጋና የእርሱ ነው፤ እርሱም በነገር ሁሉ ላይ ቻይ ነው። ከአላህ በቀር ኃይልም ብርታትም የለም፤ ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፤ እርሱንም እንጂ ሌላን አናመልክም። ችሮታ፣ ፀጋና መልካም ምስጋና የእርሱ ነው። ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፤ ከሓዲዎች ቢጠሉትም እኛ ሃይማኖታችንን ለእርሱ ብቻ አጥርተን እንገዛለን።)
((سُبْحَانَ اللَّهِ، وَالْحَمْدُ لِلَّهِ، وَاللَّهُ أَكْبَرُ (ثلاثاً وثلاثين) لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَحْدَهُ لاَ شَرِيكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ)).
(አላህ ከጉድለት ሁሉ የጠራ ነው፣ ምስጋና ለአላህ ነው፣ አላህ ታላቅ ነው።(33 ጊዜ) (ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፤ እርሱ ብቻውን ነው፣ አጋር የለውም፤ ንግሥናና ምስጋና የእርሱ ነው፤ እርሱም በነገር ሁሉ ላይ ቻይ ነው።))
بسم الله الرحمن الرحيم ﴿قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ اللَّهُ الصَّمَدُ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ وَلَمْ يَكُن لَّهُ كُفُواً أَحَدٌ﴾، بسم الله الرحمن الرحيم ﴿قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ الْفَلَقِ مِن شَرِّ مَا خَلَقَ وَمِن شَرِّ غَاسِقٍ إِذَا وَقَبَ وَمِن شَرِّ النَّفَّاثَاتِ فِي الْعُقَدِ وَمِن شَرِّ حَاسِدٍ إِذَا حَسَدَ﴾،بسم الله الرحمن الرحيم ﴿قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ النَّاسِ مَلِكِ النَّاسِ إِلَهِ النَّاسِ مِن شَرِّ الْوَسْوَاسِ الْخَنَّاسِ الَّذِي يُوَسْوِسُ فِي صُدُورِ النَّاسِ مِنَ الْجِنَّةِ وَ النَّاسِ﴾ بَعْدَ كُلِّ صَلاَةٍ.
የሚከተሉት ሦስት ሱራዎች ከዙህር፣ ከዐስርና ከዒሻ ሶላት በኋላ አንድ ጊዜ፣ ከፈጅርና ከመግሪብ ሶላት በኋላ ደግሞ ሦስት ጊዜ ይነበባሉ። [ሱራ አል-ኢኽላስ (112)] [ሱራ አል-ፈለቅ (113)] [ሱራ አን-ናስ (114)]
﴿اللَّهُ لاَ إِلَهَ إِلاَّ هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ لاَ تَأْخُذُهُ سِنَةٌ وَلاَ نَوْمٌ لَّهُ مَا فِي السَّمَوَاتِ وَمَا فِي الأَرْضِ مَن ذَا الَّذِي يَشْفَعُ عِنْدَهُ إِلاَّ بِإِذْنِهِ يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَلاَ يُحِيطُونَ بِشَيْءٍ مِّنْ عِلْمِهِ إِلاَّ بِمَا شَاءَ وَسِعَ كُرْسِيُّهُ السَّمَوَاتِ وَالأَرْضَ وَلاَ يَؤُودُهُ حِفْظُهُمَا وَهُوَ الْعَلِيُّ الْعَظِيمُ﴾ عَقِبَ كلِّ صَلاَةٍ.
ከእያንዳንዱ ሶላት በኋላ አያቱል ኩርሲን መቅራትም ሱና ነው፦ [ሱራ አል-በቀራ፣ አያ 255]
((لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَحْدَهُ لاَ شَرِيكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ يُحْيِي وَيُمِيتُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ)) عَشْرَ مَرّاتٍ بَعْدَ صَلاةِ الْمَغْرِبِ وَالصُّبْحِ.
(ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፤ እርሱ ብቻውን ነው፣ አጋር የለውም፤ ንግሥናና ምስጋና የእርሱ ነው፤ እርሱ ሕያው ያደርጋል ይገድላልም፤ እርሱም በነገር ሁሉ ላይ ቻይ ነው።(ከመግሪብና ከፈጅር ሶላት በኋላ አሥር ጊዜ))
((اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ عِلْماً نافِعاً، وَرِزْقاً طَيِّباً، وَعَمَلاً مُتَقَبَّلاً)) بَعْدَ السّلامِ مِنْ صَلاَةِ الفَجْرِ.
(አላህ ሆይ! ጠቃሚ ዕውቀትን፣ መልካም ሲሳይንና ተቀባይነት ያላቸው ሥራዎችን እጠይቅሃለሁ።)(ከፈጅር ሶላት ሰላም ካወጡ በኋላ ይባላል)