አዛንን (የሶላት ጥሪን) ሲሰሙ የሚባለው
يَقُولُ مِثْلَ مَا يَقُولُ المُؤَذِّنُ إِلاَّ فِي ((حَيَّ عَلَى الصَّلَاةِ وَحَيَّ عَلَى الْفَلَاحِ)) فَيقُولُ: ((لاَ حَوْلَ وَلاَ قُوَّةَ إِلاَّ بِاللَّهِ)).
«ሙአዚኑ እንደሚለው ይደግማል፤ ሆኖም Hayya AAalas-salah (ወደ ሶላት ኑ) ወይም hayya AAalal-falah (ወደ ስኬት ኑ) ሲል በምትኩ እንዲህ ይባላል፦ La hawla wala quwwata illa billah። ‹ከአላህ በቀር ኃይልም ብርታትም የለም።›»
يَقُولُ: ((وَأَنَا أَشْهَدُ أَنْ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَحْدَهُ لاَ شَرِيكَ لَهُ وَأَنَّ مُحَمَّداً عَبْدُهُ وَرَسُولُهُ، رَضِيتُ بِاللَّهِ رَبَّاً، وَبِمُحَمَّدٍ رَسُولاً، وَبِالْإِسْلاَمِ دِينَاً)) ((يَقُولُ ذَلِكَ عَقِبَ تَشَهُّدِ الْمُؤَذِّنِ)).
ሙአዚኑ የእምነት ምስክርነቱን ካወጀ በኋላ ወዲያውኑ ይባላል፦ «እኔም ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ፣ እርሱ ብቻውን አጋር የሌለው መሆኑን፣ ሙሐመድም ﷺ ባሪያውና መልእክተኛው መሆናቸውን እመሰክራለሁ። አላህን በጌትነት፣ ሙሐመድን ﷺ በመልእክተኝነት፣ እስልምናንም በሃይማኖትነት ወድጄ ተቀብያለሁ።»
((يُصَلِّي عَلَى النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم بَعْدَ فَرَاغِهِ مِنْ إِجَابَةِ الْمُؤَذِّنِ)).
«ከዚያም ለሙአዚኑ ጥሪ መልስ ከሰጡ በኋላ በነቢዩ ﷺ ላይ ሶላት (ሰለዋት) ማውረድ ይገባል።»
يَقُولُ: ((اللَّهُمَّ رَبَّ هَذِهِ الدَّعْوَةِ التَّامَّةِ، وَالصَّلاَةِ الْقَائِمَةِ، آتِ مُحَمَّداً الْوَسِيلَةَ وَالْفَضِيلَةَ، وَابْعَثْهُ مَقَامَاً مَحمُوداً الَّذِي وَعَدْتَهُ، [إِنَّكَ لَا تُخْلِفُ الْمِيعَادَ])).
«አላህ ሆይ! የዚህ ፍጹም ጥሪ ባለቤትና የሚቆመው የዚህ ሶላት ባለቤት ሆይ፣ ለሙሐመድ ﷺ አል-ዋሲላንና አል-ፈዲላን ስጣቸው፤ የገባህላቸውንም የተመሰገነ ስፍራ ላይ አስነሳቸው። አንተ ቃልህን አታጥፍምና።» አል-ዋሲላ፦ በገነት ውስጥ ያለ ማዕረግ። አል-ፈዲላ፦ ከፍጥረት ሁሉ በላይ የሆነ ደረጃ። የተመሰገነ ስፍራ፦ ፍጥረት ሁሉ የሚያወድሰው ስፍራ ሲሆን፣ ምርመራው እንዲፋጠንና ሰዎች ከረጅም ቆሞ መጠበቅ እንዲገላገሉ የሚደረገው የአማላጅነት ሚና ነው።
((يَدْعُو لِنَفسِهِ بَيْنَ الْأَذَانِ وَالْإِقَامَةِ فَإِنَّ الدُّعَاءَ حِينَئِذٍ لاَ يُرَدُّ)).
አንድ ሰው በአዛንና በኢቃማ መካከል ባለው ጊዜ ለራሱም ዱዓ ማድረግ ይገባዋል፤ በዚህ ጊዜ የሚደረግ ዱዓ አይመለስምና።