(بِسْمِ اللَّهِ، تَوَكَّلْتُ عَلَى اللَّهِ، وَلَاَ حَوْلَ وَلَا قُوَّةَ إِلاَّ بِاللَّهِ).
(በአላህ ስም፣ በአላህ ላይ ተመካሁ፤ ከአላህ በቀር ኃይልም ብርታትም የለም።)
3 አዝካር
(بِسْمِ اللَّهِ، تَوَكَّلْتُ عَلَى اللَّهِ، وَلَاَ حَوْلَ وَلَا قُوَّةَ إِلاَّ بِاللَّهِ).
(በአላህ ስም፣ በአላህ ላይ ተመካሁ፤ ከአላህ በቀር ኃይልም ብርታትም የለም።)
(اللَّهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ أَنْ أَضِلَّ، أَوْ أُضَلَّ، أَوْ أَزِلَّ، أَوْ أُزَلَّ، أَوْ أَظْلِمَ، أَوْ أُظْلَمَ، أَوْ أَجْهَلَ، أَوْ يُجْهَلَ عَلَيَّ).
(አላህ ሆይ! እንዳልስት ወይም እንዳላስቱኝ፣ እንዳልንሸራተት ወይም እንዳላንሸራተቱኝ፣ እንዳልበድል ወይም እንዳይበድሉኝ፣ ሞኝነት እንዳልፈጽም ወይም በሞኝነት እንዳይደረግብኝ በአንተ እጠበቃለሁ።)(መንሸራተት፦ ማለትም ሳያስቡ ኃጢአት መሥራት)
(بِسْمِ اللَّهِ وَلَجْنَا، وَبِسْمِ اللَّهِ خَرَجْنَا، وَعَلَى اللَّهِ رَبِّنَا تَوَكَّلْنَا، ثُمَّ لِيُسَلِّمْ عَلَى أَهْلِهِ).
(በአላህ ስም እንገባለን፤ በአላህ ስምም እንወጣለን፤ በጌታችንም ላይ እንመካለን።)
ከቤት በወጡ ወይም በተመለሱ ቁጥር አላህን በማውሳት መውጫዎን እና መግቢያዎን ይጠብቁ።
ምንጭ፡ ሒስን አል-ሙስሊም (የሙስሊም ምሽግ)። የአረብኛ ጽሑፍ ከትርጉም ጋር።
ከቁርኣን እና ከትክክለኛው ሱንና የተወሰዱ አዝካሮች እና ዱዓዎች ስብስብ ከሆነው ከሒስን አል-ሙስሊም የተወሰዱ ናቸው።
ቁጥሩ ከእያንዳንዱ ዚክር በላይ ይታያል። ቁጥር በማይታይበት ቦታ አንድ ጊዜ ይባላል።