([بِسْمِ اللَّهِ] اللَّهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنَ الْخُبْثِ وَالْخَبائِث).
((በአላህ ስም)። አላህ ሆይ! ከክፋትና ከክፉ አድራጊዎች ሁሉ በአንተ እጠበቃለሁ።)
6 አዝካር
([بِسْمِ اللَّهِ] اللَّهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنَ الْخُبْثِ وَالْخَبائِث).
((በአላህ ስም)። አላህ ሆይ! ከክፋትና ከክፉ አድራጊዎች ሁሉ በአንተ እጠበቃለሁ።)
(غُفْرَانَكَ).
(አንተን (አላህን) ምሕረት እጠይቃለሁ።)
(بِسْمِ اللَّهِ).
(በአላህ ስም።)
(أَشْهَدُ أَنْ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَحْدَهُ لاَ شَرِيكَ لَهُ وَأَشْهَدُ أَنَّ مُحَمَّداً عَبْدُهُ وَرَسُولُهُ..).
(ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ፣ እርሱ ብቻውን አጋር የሌለው መሆኑን እመሰክራለሁ፤ ሙሐመድም ﷺ ባሪያውና መልእክተኛው መሆናቸውን እመሰክራለሁ።)
(اللَّهُمَّ اجْعَلْنِي مِنَ التَّوَّابِينَ وَاجْعَلْنِي مِنَ الْمُتَطَهِّرِينَ)
(አላህ ሆይ! በተውበት ወደ አንተ ከሚመለሱት አድርገኝ፤ ከሚጸዱትም (ንጹሕ ከሆኑት) አድርገኝ።)
(سُبْحانَكَ اللَّهُمَّ وَبِحَمْدِكَ، أَشْهَدُ أَنْ لاَ إِلَهَ إِلاَّ أَنْتَ، أَسْتَغْفِرُكَ وَأَتوبُ إِلَيْكَ).
(አላህ ሆይ! ከጉድለት ሁሉ የጠራህ ነህ፤ በምስጋናህም አወድስሃለሁ፤ ከአንተ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ፤ ምሕረትህን እጠይቃለሁ፤ ወደ አንተም ተውበት አደርጋለሁ።)
ለዕለት ተዕለት የንጽህና እና ለሶላት ዝግጅት ጊዜያት አጫጭር ዚክሮች።
ምንጭ፡ ሒስን አል-ሙስሊም (የሙስሊም ምሽግ)። የአረብኛ ጽሑፍ ከትርጉም ጋር።
ከቁርኣን እና ከትክክለኛው ሱንና የተወሰዱ አዝካሮች እና ዱዓዎች ስብስብ ከሆነው ከሒስን አል-ሙስሊም የተወሰዱ ናቸው።
ቁጥሩ ከእያንዳንዱ ዚክር በላይ ይታያል። ቁጥር በማይታይበት ቦታ አንድ ጊዜ ይባላል።